አማርኛ
ጥያቄዎች እና መልሶች ስለ እስልምና በአማርኛ።
ኢንሻአሏህ ማለት ምን ማለት ነው?
ኢንሻአሏህ ብሎ ማለት አንድ ሙስሊም ወደፊት ሊፈፅማቸው የሚፈልጋቸውን ተግባራት በአሏህ ፈቃድ ላይ እንዲመሰረቱ ማድረግ ማለት ነው።
መልሱን አንብብእስልምና ከሳይንስ ጋር ይቃረናልን?
ቁርዓን በሳይንሳዊ ዕውቀት ማደግና በቴክኖሎጂ መምጠቅ የተነሳ በቅርብ ጊዜ ብቻ ሊደረስባቸው የቻሉ ሳይንሳዊ እውነታዎችን በውስጡ ይዟል።
መልሱን አንብብሸሐዳ ለመያዝ ምስክር መጥራት ያስፈልጎታልን?
ሸሐዳ (እስልምናን የመቀበያ ቃለ-ቀመር) ለመያዝ ምስክሮች መጥራት አስፈላጊ አይደለም። እስልምና በሰውዬውና በጌታው መካከል ያለ ጉዳይ ነውና።
መልሱን አንብብሙስሊሞች ምን ምን በዓላትን ያከብራሉ?
ሙስሊሞች ሁለት ዒዶችን (በዓላትን) ብቻ ያከብራሉ፤ በረመዷን ወር ማጠናቀቂያ የሚከበረው ዒድ አል-ፊጥርን እና በዓመታዊው የሐጅ ስነስርዓት መቋጫ ላይ የሚከበረው ዒድ አል-አድሃን (አረፋ)።
መልሱን አንብብአንድ ሰው ሙስሊም የሚሆነው እንዴት ነው?
በፅኑ እምነት "ላ ኢላሃ ኢለሏህ፤ ሙሐመዱ ረሱሉሏህ" በማለት ብቻ አንድ ሰው በቀላሉ እስልምናን ተቀብሎ ሙስሊም መሆን ይችላል።
መልሱን አንብብቁርዓንን የፃፈው ማን ነው?
ቁርዓን፥ አሏህ ለነብዩ ሙሐመድ (የአሏህ ሰላም በእርሳቸው ላይ ይሁን) በመልዕክተኛው ጂብሪል በኩል ያወረደላቸው የራሱ ቀጥተኛ ቃል ነው።
መልሱን አንብብነቢዩ ሙሐመድ ማን ናቸው?
ነቢዩ ሙሐመድ (የአሏህ ሰላም በእርሳቸው ላይ ይውረድ) ቅን፣ ፍትሃዊ፣ ሩህሩህ፣ አዛኝ፣ እውነተኛ እና ጀግና የሰው ልጅ ፍጹም ምሳሌ ነበሩ።
መልሱን አንብብእስልምና ግዳጅ ጋብቻዎችን ይፈቅዳል እንዴ?
ወንዶችም ሆኑ ሴቶች ውሃ አጣጮቻቸውን የመምረጥ መብት አላቸው፤ እናም የእንስቲቱ እውነተኛ ፈቃደኛነት ሳይታከልበት አንድ ጋብቻ ዋጋ እንደሌለው ነው የሚታሰበው።
መልሱን አንብብአሏህ ከእግዚአብሔር የተለየ አምላክ ነውን?
ሙስሊሞች የሚያመልኩት እነ ነብዩ ኖህ፣ አብርሃም፣ ሙሴ እና ኢየሱስ ያመለኩትን ተመሳሳይ አምላክ ነው። "አሏህ" የሚለው ቃል የዚህ ሁሉን ቻይ የሆነ ሐያል አምላክ የአረብኛ መጠሪያ እንጂ ሌላ አይደለም።
መልሱን አንብብእስልምና ሰዎችን ሙስሊም እንዲሆኑ በሃይል ያስገድዳልን?
ማንም ሰው እስልምናን እንዲቀበል ሊገደድ አይችልም። እስልምናን ለመቀበል፥ አንድ ሰው በሙሉ ልቡ እና በፈቃደኝነት ፈጣሪን ማመንና መታዘዝ ግድ ይለዋል።
መልሱን አንብብእስልምና የአረቦች ብቻ ነው?
እስልምና የአረቦች ብቻ አይደለም። ከሙስሊሞች አብዛኞቹ አረብ ያልሆኑ ህዝቦች ናቸው፤ እናም እስልምና መላ የሰው ዘርን የሚመለከት አለም አቀፍ ሃይማኖት ነው።
መልሱን አንብብሐላል ምግብ ምንድን ነው?
በዋናነት የአሳማ ስጋና አልኮል መጠጦች ሲቀሩ፥ ሙስሊሞች እንዲመጠቀሟቸው በአሏህ የተፈቀዱ ምግቦች ናቸው ሐላል የሚባሉት።
መልሱን አንብብሙስሊም ሴቶች ለምን ሒጃብ ይለብሳሉ?
ሒጃብ ከውጫዊ ገጽታዋ ይልቅ ውስጣዊ የመንፈስ ውበቷን በማጉላት ሴትን ልጅ የሚያጎለብት የአሏህ ትእዛዝ ነው።
መልሱን አንብብ