እስልምና ሰዎችን ሙስሊም እንዲሆኑ በሃይል ያስገድዳልን?
srpski
·
Tiếng Việt
·
Русский
·
සිංහල
·
Deutsch
·
Español
·
Français
·
አማርኛ
·
Italiano
·
Română
·
English
አሏህ በቁርዓን እንዲህ ይላል፡-
በሃይማኖት ማስገደድ የለም። ቅኑ መንገድ ከጠማማው በእርግጥ ተገለጠ። ሐሰተኛ አማልክትን የሚክድና በአሏህ የሚያምን ሰው ለርሷ መበጠስ የሌላትን ጠንካራ ዘለበት በእርግጥ ጨበጠ።
ቁራኣን - 2:256(ፍቹ ሲተረጎም)
የእስልምናን ውብ መልእክት ለሌሎች ማድረስ እና ማጋራት የሙስሊሞች ግዴታ ቢሆንም፥ ማንም ሰው እስልምናን እንዲቀበል ሊገደድ አይችልም። እስልምናን ለመቀበል፥ አንድ ሰው በሙሉ ልቡ እና በፈቃደኝነት ፈጣሪን ማመንና መታዘዝ አለበት። ስለዚህ በመሰረቱ ማንም ሰው እስልምናን እንዲቀበል ሊገደድ አይችልም (ወይም መገደድ የለበትም)።
እስቲ ቀጣዮቹን ነጥቦች ተመልከት፤
- ኢንዶኔዥያ እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሙስሊም ህዝብ አላት፤ ሆኖም ግን እስልምናን እዚያ ለማስገባት አንድም ጦርነት አልተካሄደም።
- ወደ 14 ሚሊዮን የሚጠጉ አረባዊ የቅብጥ ክርስቲያኖች አሉ፥ በአረቢያ ምድር እምብርት ለዘመናት የኖሩ።
- እስልምና ዛሬ ላይ በምዕራቡ ዓለም በፍጥነት እያደጉ ካሉ ሃይማኖቶች መካከል አንዱ ነው።
- ጭቆናን መዋጋት እና ፍትሃዊነትን ማስፋፋት ጂሃድን ለማወጅ ቅቡል ምክንያቶች ቢሆኑም፥ ሰዎች እስልምናን እንዲቀበሉ በሃይል ማስገደድ ግን ከምክንያቶቹ አንዱ አይደለም።
- ሙስሊሞች ለ800 ዓመታት ያህል ስፔንን አስተዳድረዋል፤ ነገር ግን ሰዎች ሃይማኖት እንዲለውጡ እጅ ጠምዝዘው አያውቁም።
ምንጭ:
islamicpamphlets.com
ትርጉም በ:
Abdu Ahmed