ቁርዓን ይዘቱ ስለምንድን ነው?
Русский
·
සිංහල
·
Polski
·
ไทย
·
Norsk
·
አማርኛ
·
Eesti
·
Português
·
Español
·
Tiếng Việt
·
日本語
·
中文
·
Français
·
Italiano
·
Deutsch
·
Română
·
English
ቁርዓን፥ በማሳረጊያነት የወረደው የአሏህ ቃል፥ የእያንዳንዱ ሙስሊም እምነት እና ተግባር ዋነኛ ምንጭ ነው። የሰው ልጆችን ስለሚመለከቱ ርዕሰ ጉዳዮች በሙሉ፥ ማለትም ጥበብ፣ እምነት፣ አምልኮ፣ ንግድ፣ ሕግ ወዘተ. ይዳስሣል፤ ነገር ግን መሠረታዊ መልዕክቱ በአሏህና እሱ በፈጠራቸው ፍጡራን መካከል ስላለው ግንኙነት ነው። ከዚሁ ጎን ለጎን፥ ለፍትህ ስለሚቆም ማኅበረሰብ፣ ስለጨዋ ሰዋዊ ሥነ ምግባር እና ስለትክክለኛ ምጣኔ ሀብታዊ ሥርዓት መመሪያዎችንና ዝርዝር አስተምህሮቶችን ያቀርባል።
ቁርዓን ለነብዩ ሙሀመድ ﷺ (ሰላም በእርሳቸው ላይ ይሁን) በአረብኛ ቋንቋ ብቻ መውረዱን ልብ በሉ። ስለዚህ ማንኛውም የቁርዓን ትርጉም፥ የእንግሊዝኛም ሆነ የሌላ የየትኛውም ቋንቋ፥ ቁርዓንም የቁርዓን ቅጂም ሊባል አይችልም፤ ከዚያ ይልቅ ሊባል የሚችለው የቁርዓን ፍች ትርጓሜ ብቻ ነው። ከላይ በወረደበት በአረብኛው ቋንቋ ብቻ ነው ቁርዓን የሚገኘው።
ምንጭ:
islam-guide.com
ትርጉም በ:
Abdu Ahmed