እስልምና ስለ ዝግመተ ለውጥ ምን ይላል?
አሏህ የመጀመሪያውን ሰው፥ አደም፥ በመጨረሻ ቅርፁ ፈጥሮታል - ከሰለጠኑ ጦጣዎች ቀስ በቀስ በዝግመተ ለውጥ እንደተገኘ ከሚነገረው በተቃራኒ። ሳይንስ ይህን በቀጥታ ሊያረጋግጥ አልያም ሊክድ አይቻለውም፤ ምክንያቱም የተለየ ነጠላ ታሪካዊ ሁነት - ተዓምር - ስለነበር።
ከሰዎች ሌላ ሕይወት ያላቸው ፍጡራንን በተመለከተ፥ ኢስላማዊ ምንጮች በጉዳዩ ላይ ዝምተኛ ሲሆኑ፥ አሏህ፥ በዝግመተ ለውጥም ሆነ በሌላ፥ እሱ በፈለገው መንገድ የፈጠራቸው መሆኑን ብቻ እንድናምን ይጠይቁናል።
ምንጭ:
islamicpamphlets.com
ትርጉም በ:
Abdu Ahmed