ማን ሙስሊም መሆን ይችላል?
ማንኛውም ሰው፥ የቀድሞ ሐይማኖቱ፣ እድሜው፣ ዜግነቱ፣ አልያም ብሔሩ ምንም ይሁን ምን፥ ሙስሊም መሆን ይችላል። ሙስሊም ለመሆን በቀላሉ የሚከተሉትን ቃላት ይናገሩ፡- “አሽሃዱ አላ ኢላሃ ኢለሏህ፤ ወአሽሃዱ አነ ሙሀመዱን ረሱለሏህ።” ይህ የእምነት ቃለ ምስክር “ከአሏህ በቀር ሊመለክ የሚገባው አምላክ የለም፤ ሙሐመድም መልእክተኛው መሆናቸውን እመሰክራለሁ" ማለት ነው። ይህንን ሊናገሩት እና ሊያምኑበት ይገባዎታል።
አንዴ ይህን ዓረፍተ ነገር እንደተናገሩ ወዲያውኑ ሙስሊም ይሆናሉ። ወደ ጌታዎ ለመዞር እና አዲሱን ህይወትዎን ለመጀመር፥ በሌሊትም ሆነ በቀን፥ አንድ ጊዜ ይቆይ ወይም ለአንድ ሰአት ይጠብቁ አይባሉም። ማንኛውም ጊዜ ይህን የማድረጊያ ጊዜ ነው።
እርሱ ራሱ፥ ልቅና የተገባው ይሁን፥ ይመራሃልና፥ ወደእርሱ ለመመራት የማንንም ፈቃድ ወይም የሚያጠምቅህ ካህን ወይም መሃል ገብቶ የሚያሸማግልህ አማላጅ ወይም እጅህን ይዞ መንገድ የሚያሳይህ መሪ ምንም አያስፈልግህም። እርሱ ቅርብ ነውና ወደእርሱ ፊትህን አዙር፤ እርሱ ከምታስበው ወይም ልትገምት ከምትችለው በላይ ላንተ ቅርብህ ነውና፡-
ባሮቼም ከእኔ በጠየቁህ ጊዜ (እንዲህ በላቸው)፡- "እኔ ቅርብ ነኝ፡፡ የለማኝን ጸሎት በለመነኝ ጊዜ እቀበለዋለሁ። ስለዚህ ለኔ ይታዘዙ፤ በኔም ይመኑ፤ እነሱ ሊመሩ ይከጀላልና።"
ቁራኣን - 2:186(ፍቹ ሲተረጎም)
አሏህ፥ ጥራት ይገባው፥ እንዲህ ይላል፥
አላህም ሊመራው የሚሻውን ሰው ደረቱን (ልቡን) ለኢስላም ይከፍትለታል። ሊያጠመውም የሚሻውን ሰው ደረቱን ጠባብ ቸጋራ ወደ ሰማይ ለመውጣት አንደሚታገል ያደርገዋል። ...
ቁራኣን - 6:125(ፍቹ ሲተረጎም)
ምንጭ:
islamqa.info
·
islamqa.info
ትርጉም በ:
Abdu Ahmed