አሏህ ከእግዚአብሔር የተለየ አምላክ ነውን?
עברית
·
Русский
·
Português
·
Español
·
Polski
·
Tiếng Việt
·
Deutsch
·
हिन्दी
·
srpski
·
සිංහල
·
አማርኛ
·
Français
·
Italiano
·
Română
·
English
ሙስሊሞች እነ ነብዩ ኖህ፣ አብርሃም፣ ሙሴ እና ኢየሱስ ያመለኩትን ተመሳሳይ አምላክ ያመልካሉ። "አሏህ" የሚለው ቃል በቀላሉ የሐያሉ አምላክ የአረብኛ መጠሪያ ነው። ቃሉ ጥልቅ ትርጉም ያዘለ የአረብኛ ቃል ሲሆን አንድዬውንና ብቸኛውን አምላክ የሚያመለክት ነው። በተጨማሪም አሏህ፥ አረብኛ ተናጋሪ ክርስቲያኖች እና አይሁዶች እግዚአብሔርን ለማመልከት የሚጠቀሙበት ተመሳሳይ ቃል ነው።
ነገር ግን፥ ሙስሊሞች፣ አይሁዶች እና ክርስቲያኖች በአንድ አይነት አምላክ (ፈጣሪ) ቢያምኑም ስለ እሱ በሚያቀነቅኗቸው ፅንሰ-ሀሳቦች ግን በከባዱ ይለያያሉ። ለምሳሌ፥ ሙስሊሞች እግዚአብሔር አጋሮች አሉት ወይም የ'ሥላሴ' አካል ነው የሚልን ሃሳብ ውድቅ ያደርጋሉ፤ ብሎም ፍፁምነት ሁሉን ቻይ ለሆነው ሐያል አምላክ ብቻ የሚገባ ባህርይ ነው ይላሉ።
ምንጭ:
islamicpamphlets.com
ትርጉም በ:
Abdu Ahmed